ዋና ዋና ተግባራት
በድርጅቱ የንብረት አስተዳደር ደንብ መሠረት ገቢና ወጪ ዕቃዎችን በመቆጣጠር የመጋዘኑን ሥራ ኃላፊነት ይመራል። የድርጅቱ የንብረት አስተዳደር ደንብና መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
የሥራ መደቡ ዝርዝር ተግባራት
1. የዕቃዎችን አገባብና አወጣጥ ያቅዳል፣ ይቆጣጠራል።
· በግዥ ከዋ/መ/ቤት ወይም ከሌላ ቦታ የሚመጡ አላቂና ቋሚ ንብረቶችን በመላኪያው ሰነድ መሠረት በማየት በመመርመር፣ በመቁጠር፣ በመለካት ወዘተ. በመረከብ የገቢ ሰነድ ያዘጋጃል፤
· ልዩነት ሲያጋጥም አንደ ልዩነቱ መጠን አስፈላጊውን ይፈጽማል፤
· በተዘጋጀው የወጭ ሠነድ መሠረት ወጪዎችን በአግባቡ መሆኑን ይቆጣጠራል፤
· የስቶክ ባላንስ በየቀኑ በማየት በቢን ካርድ ላይ ያስተካክላል፤
· አላቂ ዕቃዎችና አገልግሎት የጨረሱ ንብረቶችን እንዲወገዱ መረጃዎቹን ለሚመለከታቸው ያስተላልፋል፤
2. የመጋዘኑን ሥራ በበላይነት ይቆጣጠራል።
· የገቢና ወጪ እቃዎች በድርጅቱ ደንብ መሠረት በሚመለከታቸው መጽደቃቸውን ያረጋግጣል፤
· የገቢና ወጪ ሰነዶች በትክክል ይሞላል፤ ገቢ ወጪ ያደርጋል፤
· ንብረቶች በመዝገብ ላይ በትክክል መዝግቦ ይይዛል፤
· መዝገቡና ንብረቱን ያመሳክራል፤ ትክክለኛ መረጃ መኖሩን ያረጋግጣል፤
· ከተጠቃሚ ክፍሎች ጋር በመተባበር ተጨማሪ ዕቃዎች የሚጠየቁበትን ጊዜና መጠን በማጥናት ይወስናል፤
· ዕቃዎች በተጠየቁበት ጊዜና መጠን መላካቸውን ይከታተላል፤
· ዕቃዎች ተጠይቀው በምን ያህል ጊዜ መጋዘን እንደሚደርሱ ጥናት በማካሄድና የፕሮጀክቱን የሥራ ዕቅድ በሚገባ በመረዳት ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን የዕቃ ፍላጎት ዕቅድ ያወጣል፤
· ከስቶር ውስጥና ውጪ የሚቀመጡ ንብረቶችን የአቀማመጥ ስርዓት በማዘጋጀት ተግባራዊ መሆኑን ይቆጣጠራል። በተለይም ሲሚንቶ፣ ኖራ፣ ሸክላ፣ ሚስማር በቶሎ ስለሚበላሹ ከውሃ፣ ከመቀደድና ከመሳሰሉት ጉዳቶች በመከላከል የንብረት ብክነት እንዳይኖር ይቆጣጠራል፤
· አላስፈላጊ ዕቃዎች በመጋዘን እንዳይከማቹ ይቆጣጠራል፤
· የግምጃ ቤት ሠነዶች በስርዓት መቀመጣቸውን ያረጋግጣል፤
· የወጭና የገቢ ሠነዶችን እየቆረጠ ለሚመለከተው ክፍል በወቅቱ ይልካል፤
· ለድርጅቱ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች በበቂ ሁኔታ በመጋዘኑ ውስጥ ለመኖራቸው ክትትል ያደርጋል፤
· በመጋዘኑ ውስጥና አካባቢ የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችና የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና መስጫ ሳጥኖች እና ስለአጠቃቀማቸውም ከበቂ ግንዛቤ ጋር በበቂ ሁኔታ እንዲኖሩ ያደርጋል፤
· የድርጅቱ ንብረቶች በስርዓቱ መያዛቸውን ለማረጋገጥ የቁጥጥር ዘዴ ይቀይሳል፣ ለተግባራዊነቱም ክትትል ያደርጋል፤
· የንብረት ክፍሉን ዓመታዊ እቅድና በጀት ያዘጋጃል፤
· በሥሩ ያሉትን ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፤
· በተለያየ ምክንያት ከድርጅቱ የሚለቁ ሠራተኞች የሚፈለግባቸው ንብረት አለመኖሩን በማጣራት የክሊራንስ ቅጾችን ይፈርማል፤
3. ስለሥራው ክንውን በየወቅቱ ሪፖርት ያቀርባል።
· መጋዘኑን በተመለከተ ወቅታዊና የተሟላ መረጃ የሚሰጥበት መንገድ ይፈጥራል፤
· ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የሶስት ወርና ዓመታዊ የሥራ ክንውን ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፤ እንደሁኔታው የሚጠየቁ ሪፖርቶችንም አዘጋጅቶ ለጠያቂው ክፍል ያቀርባል፤
4. ሌሎች በኃላፊው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
- Degree/Diploma in Supplies & Purchasing Management
- 1/3 years & above; from which at least 2/3 years on the specified position
- Female applicants are only accepted for the post.