St. Gabriel General Hospital PLC was established in September 1996 and is the first private hospital of its kind in Ethiopia. St. Gabriel General Hospital has paved the way and continues to provide access to healthcare to both the local and international community’s here in Addis. Over the past 25 years, the hospital has served over 400,000 patients in both Outpatient and Inpatient departments.
በሆስፒታሉ የሚገኙትን የህክምናና የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ጊዜው በመከታተል ወቅቱን የጠበቀ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ዕድሳትና ክትትል እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ከአስመጪ ድርጅት ባለሙያዎች ጋር በመነጋገርም ለባለሙያዎችም ተገቢውን የአጠቃቀም ምክር ይሰጣል፣ በሆስፒታሉ ደረጃ የሚደረጉ ጥገናዎችን ያከናውናል፡፡
1. በሆስፒታሉ የሚገኙ የህክምና መሳሪያዎች የሚሰጡት አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆንና የአገልግሎት ጊዜያቸውም እንዲረዝም ወቅቱን የጠበቀ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
2. በሆስፒታሉ የሚገኙ የህክምና መሳሪያዎችና የላውንደሪ ማሽኖች የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን በማከናወን ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ መሆኑን፣ በትክክል የሚፈለገውን ውጤት እየሰጡ መሆናቸውንና እያንዳንዱ ክፍላቸው በትክክል እየሰራ መሆኑን የመሳሪያዎቹን ማኑዋል መሰረት በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀም በየጊዜው ክትትል ያደርጋል፡፡
3. እያንዳንዱ የህክምና መሳሪያና የላውንደሪ ማሽኖች ከካምፓኒው ከተሰጡ የአጠቃቀምና የደህንት መመሪያዎች አንፃር በትክክል እየተሰራበት መሆኑን ይከታተላል፣ ለተጠቃሚ ባለሞያዎችም ይህንኑ ገለፃና ድጋፍ ያደርጋል፣ ክፍተቶች ሲኖሩም የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያቀርባል፡፡
4. ሁሉም የህክምና መሳሪያንና የላውንደሪ ማሽኖች የተመለከቱ መረጃዎች- የተገዛበት ቀን፣ የተገዛበት ካምፓኒ፣ ሞዴል፣ የሚሰጠው አገልግሎት፣ የሚገኝበት ክፍል፣ መደበኛ ሰርቪስ የተደረገበትና ወደፊት ሰርቪስ የሚደረግበት ጊዜ፣ ብልሽት ገጥሞት ከሆነ የብልሽቱ ዓይነትና የተደረገለት ጥገና፣ ያስወጣው ወጪ የመሳሰሉት መረጃዎች በአግባቡ መያዝና ሪፖርት ማቅረብ፡፡
5. የተበላሹ የህክምና መሳሪያዎች ሲኖሩ ከአስመጪ ካምፓኒው ጋር ያሉ ስምምነቶችን በማይፃረር መንገድ ብልሽታቸውን በመለየት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ነገር ግን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ጥገና ያደርጋል፣ የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች ካሉም ይቀይራል፡፡ከአቅሙ በላይ ከሆነ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፡፡
6. አዳዲስ የህክምና መሳሪያዎች ሲገዙ ከሚመለከተው ካምፓኒ ባለሞያዎች ጋር የመትከልና አስፈላጊውን ሲስተም የመዘርጋት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
7. ለዲያሌሲስ ማሽኑና ለሌሎች መሳሪያዎች በትክክል ተገቢውን የኤሌክትሪክ ፓወር እያገኙ መሆኑንና በትክክል እየሰሩ መሆኑን በየጊዜው ክትትልና ሙከራ ያደርጋል፡፡
8. የዲያሌሲስ ማሽኑ በየሶስት ወሩ የማጣሪያ ፊልተር መቀየር፡፡
9. የዲያሌሲስ ማሽን ከእያንዳንዱ አገልግሎት በኋላ ለቀጣዩ አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን አስፈላጊውን የማፅዳት እና የመከታተል ስራ ይሰራል፡፡
10. የሆስፒታሉን የውሃ ማጣሪያ በየጊዜው መከታተልና ወቅቱን ጠብቆ ምርመራ እንዲደረግለት ማድረግ፡፡
11. በላቦራቶሪ የሚገኙ መሳሪያዎችና ሌሎች ልዩ ጥንቃቄ የሚፈልጉ መሳሪያዎችን በመለየትና ከሚጠቀሙባቸው ባለሞያዎች ጋር በመነጋገር በየጊዜው በትክክል መስራታቸውን ክትትል ያደርጋል፡፡
12. ለህክምና መሳሪያዎች ተጠቃሚ ባለሙያዎች በየጊዜው ስለመሳሪያዎቹ ባህሪ፣ ውጤታማ የአጠቃቀም መንገዶችና በየጊዜው ስለሚኖሩ ወቅታዊ ለውጦች ተገቢውን ማብራሪያና ስልጠና ይሰጣል፡፡
13. ከባለሙያዎች ጋር በመነጋገር የህክምና መሳሪያዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ከማሽኖቹ የሚገኙ አጠራጣሪ ውጤቶችን በመለየት በራሱ ወይም ከሚመለከተው አስመጪ ድርጅት ጋር በመነጋገር አፋጣኝ መፍትሄ ይወስዳል፡፡
Requirements