ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት
1 ለድርጅቱ አገልግሎት የሚያስፈልጉ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች ባለው ፍጆታና መለኪያ ዘዴ (minimum stock Level, reorder Level, Safety Stock Level etc.) መሠረት ወደ ዋናው ፋርማሲ ወጭ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
2 ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የተገዙ መድኃኒቶችና መገልገያ መሣሪያዎችን ከጥያቄው ጋር በማገናዘብ ከመጋዘን ከሌሎች ጋር በየተራ ወጭ ያደርጋል፣
3 የተገዙና ወጪ የተደረጉ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በተገቢዎቹ የጠቀሜታ ጊዜ ውስጥ በስራ ላይ እንዲውሉ ለክፍሉ ኃላፊ ያሳውቃል (ከ6 ወር በፊት)፣
4 ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተገዙ መድኃኒቶችና መገልገያ መሣሪያዎች የመጠቀሚያ ጊዜን በመሠረታዊ የInventory መርሆዎች መሠረት ይከታተላል፤ በመመዝገብና በፋይል በመያዝ ለኃላፊው ያሳውቃል፣
5 ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን በተለየ የብረት ሳጥን ቆልፎ ያስቀምጣል፤ ሲታዘዙ የታዘዘበትን የመድኃኒት ማዘዣዎች ፋይል አድርጐ ያስቀምጣል፤ በቀዝቃዛ ቦታ መቀመጥ የለባቸውንም በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ እንዲቀመጡ ያደርጋል መርዛማነትና ተቀጣጣይነት ባሕሪ ያላቸውን መድኃኒቶች በተለየ ሁኔታ በጥንቃቄ ያስቀምጣል፣
6 በመድኃኒት መጋዘን ውስጥ የሚገኙ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን ተከታትሎ በማየትና በመጠየቅ ከመጋዘን ወደ ዋና ፋርማሲ ወጭ ሆኖ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ይከታተላል፣
7 በቅርብ አለቃው በደረጃው የሚሰጠውን ተመሳሳይ ተግባሮች በብቃት ያከናውናል እንዲሁም የመድኃኒት ኃላፊው በሌለበት ቦታ ተተክቶ ይሠራል፡፡
Let Employers Find You
Featured Jobs